ሥራችን
የጋራ ውትወታ
- ከፖሊሲ አውጪዎች ፣ የመንግሥት ተቋማት ፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ፕሬስ ነፃነት የሚጠብቁ የህግ ማሻሻያዎች ላይ መሳተፍ።
- በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ጠንካራ የሆኑ ሕጋዊ ስርዓቶችን ለመቅረጽ መስራት።
- የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን የደህንነት ስጋቶች በክልላዊ ፣ በሃገራዊ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ እንዲሰማ በማድረግ ፣ ዓለም አቀፍ ወንድማማችነት እና ትኩረት ማረጋገጥ።
ፈጣን ምላሽ እና ጥበቃ
- ለአደጋ የተጋለጡ ጋዜጠኞች የሕግ ድጋፍ፣ የገንዘብ እርዳታ፣ ጊዜያዊ ቦታ ለውጥ እና የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎቶችን ጨምሮ የተቀናጀ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ መስጠት።
- ጋዜጠኞች በታሰሩ፣ በተደበደቡ ወይም በተጠቁ ጊዜ በወቅቱ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ጥምረት ማቋቋም እና ማስተባበር።
- ለአደጋ የተጋለጡ ጋዜጠኞች አገልግሎት የሚሰጥ የደህንነት መመሪያዎች እና የአደጋ ጊዜ መረጃ መቀበያ ቁጥሮችን በማዘጋጀት ከአጋሮች ጋር በመተባበር መስራት።
ክትትል እና ሰነድ ማዘጋጀት
- በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙት የመብት ጥሰቶች መከታተል ፣ መመዝገብ ፣ መተንተን እና ሪፖርት ማድረግ።
- በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ወቅታዊ የሆኑ የደህንነት ሪፖርቶችን ማዘጋጀት።
- በሁሉም ደረጃዎች ግንዛቤ ለማሳደግ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን አጋሮች ጋር መስራት።
አቅም ግንባታ እና ስልጠና
- በአካላዊ ደህንነት፣ በይነ-መረብ ደህንነት፣ የሕግ መብቶች እና በጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ ማቅረብ።
- በግጭት ወቅት እና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የተለዩ ድጋፎችን ማድረግ።
- በተለያዩ ማኅበራት እና ክልሎች የሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል የእርስ-በእርስ ግንኙነቶች እንዲዳብሩ ማመቻቸት።
ጾታ-ተኮር እርምጃዎች
- ሴት ጋዜጠኞችን በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም በሥራ ቦታ የሚያጋጥማቸውን አደጋ ለመከላከል በልዩነት የተሰሩ ፕሮግራሞችን መተግበር።
- በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሴቶችን እኩል የሆነ የመሪነት ድርሻ የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩም ሆነ እንዲሻሻሉ መስራት።
- ለሴት ጋዜጠኞች ተሞክሮዎችን ለመጋራት ፣ ሀብቶችን ተደራሸ ለማድረግ እና የጋራ ጥምረቶችን ለመገንባት ደህንነቱ የተጠበቀ ከባቢን ማመቻቸት።
ትብብር እና ጥምረት
- የተለያዩ የጋዜጠኞች ማኅበራትን በማቀናጀት የጋራ ስራዎችን መስራት እና ሀብቶችን መጋራት እንዲችሉ መከወን።
- በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱትን አደጋዎች ለመከላከል ከክልላዊ እና ብሔራዊ አጋሮች ጋር ያለን ግንኙነት ማጠናከር።
- የወንድማማችነት ባህልን ማጎልበት፣ ማንኛውም ጋዜጠኛ የጥቃት ሰለባ እንዳይሆን መስራት።
በእነዚህ ፕሮግራሞች አማካኝነት፣ CSoJ ለስጋቶች ምላሽ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን የጋዜጠኞችን ደህንነት እና ጽናት የሚያረጋግጡ የረጅም ጊዜ መዋቅሮችን ለመገንባትም ያለመ ነው።