የጋራ ውትወታ

  • ከፖሊሲ አውጪዎች ፣ የመንግሥት ተቋማት ፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ፕሬስ ነፃነት የሚጠብቁ የህግ ማሻሻያዎች ላይ መሳተፍ።
  • በጋዜጠኞች ላይ ጥቃት የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ጠንካራ የሆኑ ሕጋዊ ስርዓቶችን ለመቅረጽ መስራት።
  • የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን የደህንነት ስጋቶች በክልላዊ ፣ በሃገራዊ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ እንዲሰማ በማድረግ ፣ ዓለም አቀፍ ወንድማማችነት እና ትኩረት ማረጋገጥ።

ፈጣን ምላሽ እና ጥበቃ

  • ለአደጋ የተጋለጡ ጋዜጠኞች የሕግ ድጋፍ፣ የገንዘብ እርዳታ፣ ጊዜያዊ ቦታ ለውጥ እና የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎቶችን ጨምሮ የተቀናጀ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ መስጠት።
  • ጋዜጠኞች በታሰሩ፣ በተደበደቡ ወይም በተጠቁ ጊዜ በወቅቱ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ጥምረት ማቋቋም እና ማስተባበር።
  • ለአደጋ የተጋለጡ ጋዜጠኞች አገልግሎት የሚሰጥ የደህንነት መመሪያዎች እና የአደጋ ጊዜ መረጃ መቀበያ ቁጥሮችን በማዘጋጀት ከአጋሮች ጋር በመተባበር መስራት።
i

ክትትል እና ሰነድ ማዘጋጀት

  • በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙት የመብት ጥሰቶች መከታተል ፣ መመዝገብ ፣ መተንተን እና ሪፖርት ማድረግ።
  • በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ወቅታዊ የሆኑ የደህንነት ሪፖርቶችን ማዘጋጀት።
  • በሁሉም ደረጃዎች ግንዛቤ ለማሳደግ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን አጋሮች ጋር መስራት።

አቅም ግንባታ እና ስልጠና

  • በአካላዊ ደህንነት፣ በይነ-መረብ ደህንነት፣ የሕግ መብቶች እና በጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ ማቅረብ።
  • በግጭት ወቅት እና ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የተለዩ ድጋፎችን ማድረግ።
  • በተለያዩ ማኅበራት እና ክልሎች የሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል የእርስ-በእርስ ግንኙነቶች እንዲዳብሩ ማመቻቸት።

ጾታ-ተኮር እርምጃዎች

  • ሴት ጋዜጠኞችን በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም በሥራ ቦታ የሚያጋጥማቸውን አደጋ ለመከላከል በልዩነት የተሰሩ ፕሮግራሞችን መተግበር።
  • በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሴቶችን እኩል የሆነ የመሪነት ድርሻ የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩም ሆነ እንዲሻሻሉ መስራት።
  • ለሴት ጋዜጠኞች ተሞክሮዎችን ለመጋራት ፣ ሀብቶችን ተደራሸ ለማድረግ እና የጋራ ጥምረቶችን ለመገንባት ደህንነቱ የተጠበቀ ከባቢን ማመቻቸት።

ትብብር እና ጥምረት

  • የተለያዩ የጋዜጠኞች ማኅበራትን በማቀናጀት የጋራ ስራዎችን መስራት እና ሀብቶችን መጋራት እንዲችሉ መከወን።
  • በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱትን አደጋዎች ለመከላከል ከክልላዊ እና ብሔራዊ አጋሮች ጋር ያለን ግንኙነት ማጠናከር።
  • የወንድማማችነት ባህልን ማጎልበት፣ ማንኛውም ጋዜጠኛ የጥቃት ሰለባ እንዳይሆን መስራት።

በእነዚህ ፕሮግራሞች አማካኝነት፣ CSoJ ለስጋቶች ምላሽ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን የጋዜጠኞችን ደህንነት እና ጽናት የሚያረጋግጡ የረጅም ጊዜ መዋቅሮችን ለመገንባትም ያለመ ነው።