ኅብረት ለጋዜጠኞች ደህንነት በኢትዮጵያ በሰባት መስራች የጋዜጠኞች ማኅበራት ተመስርቶ የተቋቋመ ሲሆን እያንዳንዳቸው በኢትዮጵያ ሚዲያ መስክ የተለያዩ ክልሎችን ፣ ዘርፎችን እና ማህበረሰቦችን ይወክላሉ። እነዚህ ማኅበራት በጋራ ያላቸውን የዳበሩ ተሞክሮዎችን ፣ የተለያዩ ማህበረሰብ እይታዎችን ከጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር መርሆች ጋር በማዛመድ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞችን መብት ለመጠበቅ በጋራ የመሰረቱት ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር

በሐዋሳ የተመሠረተ ፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ለሚሰሩ ጋዜጠኞች መብት እና ደህንነት የቆመ እየሠራ የሚገኝ።

የሶማሌ ጋዜጠኞች ማኅበር

በጅግጅጋ የተመሠረተ እና በሶማሌ ክልል የሚገኙ ጋዜጠኞችን በመወከል ያገለግላል። የፕሬስ ነፃነትን ለመጠበቅ እና ለጥቃት የተጋለጡ ጋዜጠኞች ቀጥተኛ ድጋፍ በመስጠት ይሠራል።

የምስራቅ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር

በሐረር የተመሠረተ ፣ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን አባል በማድረግ ፤ የሙያ አቅም እና ደህንነት ማጠናከር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን የሚሰራ።

ሚዛን ፕሮፌሽናል ጋዜጠኞች ማኅበር (ሚዛን)

በአዲስ አበባ የተመሠረተ ፣ በኢትዮጵያ ሚዲያ ዘርፍ ውስጥ የሙያ ብቃት ያላቸው ጋዜጠኞች እንዲጎለበቱ ይሠራል።

የኢትዮጵያ ሴት መገናኛ በዙሃን ባለሙያዎች ማኅበር

በአዲስ አበባ የተመሠረተ ፣ ለሴት ጋዜጠኞች ድምጽ በመሆን የሥራ ቦታ እኩልነት እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶቸን በመታገል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ መገናኛ በዙሃን ፕሮፌሽናሎች ማኅበር

በአዲስ አበባ የተመሠረተ ፣ የመገናኛ በዙሃን ባለሙያዎችን በአባልነት በማሰባሰብ ፣ የፕሬስ ነፃነትን ለመጠበቅ ይሠራል።

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር

በአዲስ አበባ መሥሪያ ቤት ያለው ፣ የይዘት ጠባቂዎች የሆኑትን አርታዒያን በመወከል ለገለልተኝነታቸው ፣ ለነፃነታቸው እና የሙያ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ይሰራል።

እነዚህ ሰባት መስራች አባላት አንድ ላይ ሆነው የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች ለመጠበቅ እና ለማብቃት በሚደረገው ተልዕኮ አንድ ሆነው የCSoJ የጀርባ አጥንት ይሆናሉ።