ሥራችን
ኅብረት ለጋዜጠኞች ደህንነት በተቀናጀ መልኩ በመላው ኢትዮጵያ የጋዜጠኞችን ደህንነት ለማጠናከር የውትወታ ፣ ጥበቃ ፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ፣ እንዲሁም አቅም ግንባታ ስራዎችን ለማስተባበር እና ለመምራት የተመሰረተ ነው።
የጋራ ውትወታ
ከፖሊሲ አውጪዎች ፣ የመንግሥት ተቋማት ፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ፕሬስ ነፃነት የሚጠብቁ የህግ ማሻሻያዎች ላይ መሳተፍ።
ፈጣን ምላሽ እና ጥበቃ
ለአደጋ የተጋለጡ ጋዜጠኞች የሕግ ድጋፍ፣ የገንዘብ እርዳታ፣ ጊዜያዊ ቦታ ለውጥ እና የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎቶችን ጨምሮ የተቀናጀ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ መስጠት።
ክትትል እና ሰነድ ማዘጋጀት
በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙት የመብት ጥሰቶች መከታተል ፣ መመዝገብ ፣ መተንተን እና ሪፖርት ማድረግ።
አቅም ግንባታ እና ስልጠና
በአካላዊ ደህንነት፣ በይነ-መረብ ደህንነት፣ የሕግ መብቶች እና በጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ ማቅረብ።
ጾታ-ተኮር እርምጃዎች
ሴት ጋዜጠኞችን በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም በሥራ ቦታ የሚያጋጥማቸውን አደጋ ለመከላከል በልዩነት የተሰሩ ፕሮግራሞችን መተግበር።
ትብብር እና ጥምረት
የተለያዩ የጋዜጠኞች ማኅበራትን በማቀናጀት የጋራ ስራዎችን መስራት እና ሀብቶችን መጋራት እንዲችሉ መከወን።
አባልነት
የኅብረት ለጋዜጠኞች ደህንነት በኢትዮጵያ አባልነት ለሁሉም በሕግ መሰረት የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበራት ከሀሳባችንና ከተልእኳችን ጋር ለሚስማማ በሙሉ ተቀባይነት አለው።
ይቀላቀሉን እና አባል ይሁኑ
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የጋዜጠኞች ማህበራት የኅብረታችን አካል እንዲሆኑ እናበረታታለን። በጋራ በመሆን ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የበለጠ ነጻ እና ጠንካራ የሚዲያ ሁኔታን መገንባት እንችላለን።
ኅብረቱን በመቀላቀል ማህበራት የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ፦
- በብሔራዊ ፣ ክልላዊ እና አለም አቀፍ ደረጃ የውትወታ እና የውክልና የጋራ መድረክ።
- በስልጠና ፕሮግራሞች ፣ በማሠልጠኛ መመሪያዎች እና ስራዎች እንዲሁም የጋራ ሀብቶች ተደራሽነት።
- በፈጣን ምላሽ ማሰራጫ ስልቶች እና በጥበቃ አሰራሮች ውስጥ የመሳተፍ እድሎች።
- በፕሬስ ነፃነት እና በጋዜጠኞች ደህንነት ላይ በቁጥጥር እና ሪፖርት ስርዓቶች ውስጥ መካተት።
- በጋራ ትብብር እና ልምድ መጋራት በኩል ጠንካራ ግንኙነት እና አጋርነት ጥምረቶች ተሳትፎ።